Thursday, 26 April 2018

Agilla Videos (copy)

ወደ አባቶች ዙር።

የከፋ እንዳይመጣ
አንድነቱን አምጣ።
እምነትን ፍጠር
በአንድ ላይ ምከር።
ጥያቄም ይጠየቅ ከልብ ይብሰልሰል
መሰረት እንዲኖር የጠበቀ ውል።
ኢትዮጵያ የሚለው ጨርሶ እንዳይጠፋ
ትውልድ እንዳይረግምህ  አንገት እንዳይደፋ
እንደምንም ብለህ በአንድነቱ ግፋ።
ቀበቶህን አጥብቅ ወደ አባቶች ዙር
መፍትሄ እሱ ነው ለማለፍ ችግር
ወደ ድል ሚወሰደው ያለ ጥርጥር።

Remember Me

       

Advert1

Agilla Videos